You are currently viewing የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ እና አልማ ኮን ህንጻ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች 11 ሚሊዮን ብር ሽልማት አበረከቱ ፡፡

የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ እና አልማ ኮን ህንጻ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች 11 ሚሊዮን ብር ሽልማት አበረከቱ ፡፡

የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ እና አልማ ኮን ህንጻ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች 11 ሚሊዮን ብር ሽልማት አበረከቱ ፡፡
——–//////——-
የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የገቢ ማስገኛ ተቋማት የሆኑት የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ እና አልማ ኮን ህንጻ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 451 ተማሪዎች ሽልማት አበርክተዋል።
ሽልማቱን ያበረከቱት በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የማክበር እና የማበረታታት ልዩ ሥነ-ሥርዓት በድምቀት በተካሄደበት ወቅት ነው ።
በዕውቅና ሥረዓቱ ላይ የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የገቢ ማስገኛ ተቋማት የሆኑት የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ እና አልማ ኮን ህንጻ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋራ በመሆን ለ451 ተማሪዎች የ11 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት አበርክተዋል፡፡ በዚህም ለትምህርት ዘርፍ ያላቸውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት በተግባር አሳይተዋል።
ተቋማቱ የሚያገኙትን ትርፍ ለማህበራዊ ድጋፍ የማዋል ኣላማን ይዘው የተደራጁ በቀጣይ የሚያገኙትን ትርፍ ለልማት ስራ በማዋል የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ የአልማ የገቢ ማስገኛ ተቋማት ናቸው ፡፡
የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጆች አቶ ታደሰ መላሽ እና አልማ ኮን ህንጻ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አሰፈጻሚ አቶ ሰጥቷል ደሳለኝ በቀጣይም ድርጅቶቹ ከትርፋቸው ለማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ የማድረጉን ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
ከሸዋ ሮቢት ተማሪ በረከት ንጉሴ (507 ነጥብ) ፣ የተማሪ ኤፍራት ምትኩ (540.92 ነጥብ)እና ወላጅ እናት የሆኑት ዶ/ር ነጻነት ጌጤን ጨምሮ በርካታ ተሸላሚዎች እና ወላጆች በሰጡት አስተያየት አልማ በትምህርቱ ዘርፍ ከገጠር እስከ ከተማ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦና ድጋፍ አድንቀዋል።
ድጋፍ ያደረጉ የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ እና አልማ ኮን ህንጻ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአልማ ስኬት መገለጫዎች መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይም ለአልማ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
የተደረገው የገንዘብ ሽልማት ተማሪዎች ለበለጠ ስኬት እንዲተጉ የሚያነሳሳና ድርጅቶቹ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በመቅረጽ ረገድ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያሳይ ነው ፡፡
አማራ ልማት ማህበር ከአባላት የሚያገኘውን ሃብት ሙሉ በሙሉ ለልማት እያዋለ የሚገኝ አገር በቀል የልማት ማህበር ሲሆን ጎን ለጎን ደግሞ የቢዝነስ ተቋማትን በማቋቋም የሚያገኘውን ትርፍ ለህዝብ ልማት ለማዋል ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

Leave a Reply